
"ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል" (1ኛ ዮሃንስ 4:11) በነዚህ ሶስት አጫጭር ደብዳቤዎች፡ የተወደደው ደቀመዝሙር ዮሃንስ በተለያዩ ጊዜያት፣ አስራ-ሶስት ጊዜ የሚሆን ለአንባቢዎቹ እርስ በእርሳቸው እንዲዋደዱ ያበረታታቸው ነበር። እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን/ 1ኛ ዮሃንስ 4:19 እርስ በእርሳችን መዋደድ የምንችለው ከእግዚአብሔር (ልጁን ለኛ ብሎ ከሰዋልን) ካገኘነው ፍቅር የተነሳ ነው። "እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት" (2ኛ ዮሃንስ 1:6) በነዚህ ደብዳቤዎቹ ዮሃንስ በመታዘዝና በፍቅር መሃከል ያለውን ጥልቅ ትስስር አስረድቷል። ለቀደምት ቤተ፟ክርስቲያን በእግዚአብሔር ትእዛዞች ላይ ታምና እንድትቆም ያበረታታ እንደነበር እኛንም ድግሞ አሁን ያበረታታናል። በመታዘዛችን ምክንያት ሌሎችን መውደድና እግዚአብሔር ለምድሪቷ ያለውን ፍቅር ማሳየት እንችላለን። ፍቅርን ማወቅ፡ የ 1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ ዮሃንስ ጥናት ስለ 1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ ዮሃንስ ደብዳቤዎች ያስሳል ደግሞም የክርስቶስ ተከታዮች ለሆኑት በእግዚአብሔር ፍቅር እንዲጸኑ ያበረታታል። ዮሃንስ ስለ እርስ በእርስ መዋደድ የስጠው ምክር ለመጀመሪያ ክፍለዘመን ለነበሩ አማኞች አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ለአኛም ጭምር አስፈላጊ ነው። ይሄ ጥናት፦ የክርስቶስ ፍቅር እኛን ብቻ ሳይሆን የሚቀይረው የእሱ ትዛዞችን በመከተላችን ደግሞ እንዴት አድርጎ ምድርን እንደሚቀየር ያስረዳል። በዖንላይን የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ወይም በላቭ ጎድ ግሬትሊ አፕ ከኛ ጋር እንደምትሳተፊ ተስፋ እናደረጋለን። በሁልቱም ቦታ አንድ አይነት የፍቅርን ማወቅ ትምህርት፣ በየሰኞ፣ ዕሮብ እና ዓርብ የሚወጣ ብሎግስ፣ አስፍተሽ ልታይበት ይምትችይው ዕለታዊ የእዚአብሔር ቃልና እንደ እየሱስ ለመኖርና ለማፍቀር ስትማሪ በፍቅር የተሞሉ የሚያበረታቱሽ የሴቶች ማህበር ታገኛለሽ።
Page Count:
112
Publication Date:
2021-12-07
Publisher:
Blurb, Incorporated
ISBN-10:
1006135928
ISBN-13:
9781006135927
No comments yet. Be the first to share your thoughts!